ድምጽዎን በታሪክዎ ውስጥ ያግኙ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ….ድረ ገፃችንን ስለጎበኛችሁ ከልብ እያመሰገንን አፈታሪክ Afetarik እንዴት እና ለምን ለመስራት እንዳሰብኩ ላጫዉታችሁ ።

    ነገሩ የጀመረዉ በ2007 ወደ አዲስ አበባ ከሰባት ዓመት ገደማ ብኋላ ስመለስ ነዉ።ከተማዋን እንደ አዲስ የጎበኘሁበት ጊዜ ነበርበዚያን ጊዜ የአዲስ አበባ ግንባታዎች የባቡር ፕሮጀክቶችን እና በግንባታ ላይ ያሉ ብዙ ሕንፃዎችን ያካተተ ነበር።በጣም ብዙ ነገሮች ተለዉጠዋል በመገረም ከአዲስ አበባ ዉጪ ያለሁ እስኪመስለኝ ድረስ። ተወልጄ ያደኩባት ከተማ እማቃቸዉ መንገዶች ፎቆች እየተለወጡ መምጣታቸዉን ተገነዘብኩኝ ።የሆነ ነገር ማረግ እንዳለብኝ የወሰንኩት ሜክሲኮ አካባቢን እና መስቀል አደባባይ ላይ ያለዉን የባቡርድ መንገድ ካየሁ ብኋላ ነዉ ።

   የወላጆቻችንን ሰሜት ተረዳሁት ልጅ እያለሁ ወይም ከ20፣30 ዓመት በፊት ነገሮች በጣም ቆንጆ ነበሩ ሲሉ አዲሱን ነገር ጠልተዉት ሳይሆን የሚያዉቁት ነገር ሁሉ አየተለወጠባቸዉ ትዝታቸዉን እሚያነቃቁት ነገሮች ስለሌሉ እየናፈቁ ነዉ።ሁላችንም ወላጆቻችን፣አያቶቻችን ወይም ዘመዶቻችን ታሪክ ነግረዉናል። ሰለአደጉበት ቦታ እንዴት እንደነበረ፣እንዴት እንደተቀየረ ።በጣም አሰማምረዉ ኩለዉ የተናገሩ ነው ሚመስለን የነበረው። አንድ አንዴም እውነት መሆኑ ያጠራጥረናል።የተመዘገበ ነገር አለመኖሩ እንድንጠራጠር ያደርጋል።የኔም ታሪኮች ታአማኒነታቸዉን ሊያጡ እንደሚችሉ ባወኩ ጊዜ መዝግቦ ማስቅመጥ አስፈላጊ መሆኑን ተረዳሁ።

    መፍትሄዉም የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ትዝታዎቻቸውን እና ታሪኮቻቸውን በቀላሉ ለመመዝገብ የሚያስችል መንገድ እና እነዚህን መዝገቦች ደግሞ በቀላሉ ለማግኘት የሚቻልበትን መንገድ መፍጠር ነበር።አፈታሪክ Afetarik ለዚህ ጥሩ መፍትሄ ይሆናል ብለን እናስባለን።የአዲስ አበባ ታሪኮች በነዋሪዎቹ መቀየር እና በትልልቆቹ  ከዚህ አለም በሞት መለየት አብሮ እየጠፉ ስለሚሄዱ መመዝገብ የግድ ነው።ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለሰፈራቸዉ ስያሜ ታሪኮች መዝጋቢ እንዲሆኑ የሚረዳ ነው። የአንዳዱ ሰፈር ስያሜ ከጀርባው ያለዉን ታሪክ መገመት ቀላል ነዉ።ያንዳዱ ደግሞ ሚስጥራዊ ነው።አፈታሪክ Afetarik ሁላችንንም ታሪክን መዝግቦ ማስቀመጥን ባህል ለማረግ የሚረዳ ነው። ታሪኮችን፣ምስሎችን እና ሌሎችንም ስለ ከተማችን የሚሰበስብ ድረ ገጽ ነው።

    የወደፊት አላማችን በየአመቱ የሰፈር ታሪኮችን ስብስብ የያዘ በድረ ገጻችን ያጠራቀምናቸውን ታሪኮችንና ምስሎችን በመጠቀም መጽሃፍ ለማሳተም ሲሆን።አሳትሞ በመጻህፍት ቤት ውስጥ ወይም መደብሮች በቀላሉ እንዲገኙ ለማረግ ነው።የወደፊት ትልቁ አላማችን የሚሆነው የነዚህን ሰፈሮቹ ታሪክ በደንብ ለመያዝ ፣የቱሪዝም ሰርቪሶችን ለመገንባት እናም የአገሪቷ ነዋሪዎችን የዉጭ ቱሪስቶችን ወይም ኤክስፓትርየት የነዚህን ታሪኮች አስደናቂ ቦታዎችን ለማሳየት ይረዳል ብለን እናምናለን።

አዲስ አበባ ስራችንን ለመጀመር የመረጥንበት ምክንያት ተወልጄ ያደኩበት ቦታ ሲሆን።ነገር ግን አፈታሪክ Afetarik ወደ ሌላ ከተሞች እንዲስፋፋ ምኞታችን ነው።እንዲሁም በበመላው አሃጉር።

                         

                                                                                                                              - መዓረግ ተስፋዝጊ

 ድምጽዎን በታሪክዎ ውስጥ ያግኙ

©2018 BY AFETARIK.